Ethiopia

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን

ይህ የአይንትራክት ፍራንክፈርት የእግር ኳስ ክለብ የኢትዮጲያ ደጋፊዎች ማህበር ገፅ ነው፡፡ የማህበራችን የኢትዮጲያ ሊቀመንበር አቶ ሙህሲን ደረባቸው ሲሆን ምክትል ሊቀመንበርና በገፃችን ላይ የሚተላለፈውን መልዕክት በማዘጋጀት ለእናንተ የሚያደርሱት ዶ/ር በረከት ፀጋዬ ናቸው፡፡ ዶ/ር በረከት ፀጋዬ በሙያው የህክምና ዶክተር ሲሆን በሃገሪቷ ዝነኛና ተነባቢ በነበረችው ኢንተር ስፓርት ጋዜጣ ፍሪላንሰር ሪፓርተር ሆኖ ከማገልገሉ በላይ በአሁኑ ወቅትም በADDIS INSIGHT የመዝናኛ ድህረ ገፅ የስፓርት “ብሎገር፤” FOOTBALL FIRST በሚል የፌስቡክ ማህበራዊ ገፅ admin ሆኖ በእግር ኳስ ጋዜጠኝነት ዙሪያ ያለውን ልምድ እያካበተ የሚገኝ ወጣት ባለሙያ ነው።

በመላው አለም ብሎም በሃገራችን ኢትዮጵያ አይንትራክት እና የጀርመኗን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ፍራንክፈርት ለማስተዋወቅ እንዲሁም ደጋፊዎችን ለማስተሳሰር ተብሎ በተከፈተው የደጋፊዎች ገፅ ( Fan Page) የኢትዮጵያ ክፍል በቅርብ ቀን: ~ ስለ አይንትራክት ፍራንክፈርት 10 ነጥቦች ~ የጨዋታ ቀን መርሃ ግብር ~ ክለባዊ ዳሰሳ (preview) ~ ቆይታ ከኒኮ ኮቫች ጋር ~ ውጤቶች፣ የደረጃ ሰንጠረዥ እና ሌሎች

 

10 ነጥቦች ስለ አይንትራክ ፍራንክፈርት

ሁለት ጊዜ የጀርመን ሻምፒዮን ሆኗል። (እ.ኤ.አ 1932፣ 59) እንዲሁም 1 ጊዜ የቡንደስሊጋውን ዋንጫ ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በ2011/12 የውድድር አመት 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ውጤት በከፍተኛነቱ ይታወሣል።

በአህጉራዊ መድረክ እ.ኤ.አ. 1979/80 የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫን በአሁኑ አጠራር ዩሮፓ ሊግን ያሸነፉ ሲሆን በ1960 የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ የነበሩበት በትልቅ ደረጃ የተቀመጡ የክለቡ የአውሮፓ ክብሮች ናቸው።

ከጁላይ 2005 አንስቶ መቀመጫውን ፍራንክፈርት ሄሲ በተባለ ቦታ ያደረገው የክለቡ ስታዲዮም ከስፓንሰርሺፕ ስምምነት ጋር ተያይዞ ‘ኮሜርዝባንክ አሬና’ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን 51,500 ተመልካቾችን በወንበር ያስተናግዳል።

ንስሮቹ በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩ ሲሆን ይህንን ስያሜ በተለይም በ 90ዎቹ መጨረሻ ታላላቆቹን ቡድኖች ሳይቀር ማሸነፍ በመቻላቸው መገናኛ ብዙሃን በስፋት ይጠቀሙበት እንደነበር የክለቡ ኦፊሴልያዊ ድህረ ገፅ ያወሳል።

እ.ኤ.አ በ 2011/12 ቡንደስሊጋ የውድድር አመት የፍራንክፈርት ደርቢ በአይንትራክት እና ኤፍ.ኤስ.ቪ ፍራንክፈርት መካከል ከ50 አመታት በኃላ ተካሂዶ ነበር። በደርሶ መልስ ፍልሚያ አይንትራክት ድል ሲቀናው በአጠቃላይ የርስ በርስ 8 ጊዜ ግንኙነቶች በ7ቱ አይንትራክት ድል ማድረግ ሲችል ቀሪው 1 ግጥሚያ በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሆኗል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ክለቡ በመጀመሪያው አጋማሽ ተስፋ ሰጪ ፋክክር ማድረግ ቢችልም በሁለተኛው ዙር ባጋጠመው የውጤት መንሸራተት አመቱን በ11ኛ ደረጃ ለማጠናቀቅ ተገድዋል። በ2015-16 ሲዝን የመውረድ አደጋ አንዣቦበት ቢቆይም በደርሶ መልስ ግጥሚያ ለጥቂት ከመውረድ የተረፈበት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነበር።

ካለፋት 5 ተከታታይ የውድድር አመቶች ለ3 ጊዜ ያህል ግዚፉ ጀርመናዊ አጥቂ ማክስ ማየር የክለቡ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኖ አመቱን ያጠናቀቀ ሲሆን አምና ሜክሲኮያዊው ማርክ ፋቢያን ያስቆጠራቸው 7 ግቦች የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተብሎ እንዲሰየም ረድቷል።

ክለቡ ለአዲሱ የውድድር አመት ቅድመ ዝግጅት መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካና ጣልያን በማድረግ ልምምዱን ሲሰራ ቆይቷል። ክሮሽያዊው ወጣት አሰልጣኝ ጠንካራና ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት በሚያደርገው ሂደት ወደ 8 ያህል የወዳጅነት ግጥሚያዎችን ማድረግ ሲችል የከተማ ተቀናቃኙን FSV ፍራንክፈርትን አስተናግዶ 5-2 የረታበት በከፍተኛነቱ የሚጠቀስ ድል ሆኖ ተመዝግቧል።

የ2017/18 ቡንደስሊጋ ሲዝን ከመከፈቱ አስቀድሞ በጀርመን ዋንጫ ፍራንክፈርት የዲቪዝዮኑን ቢድን ኤርዳንትብሪክትን በመግጠም አመቱን ይከፍታል። የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውንም ፍራይበርግን ከሜዳው ውጪ በማስተናገድ ይጀምራል።

እ.ኤ.አ በ1899 አ.ም የተመሰረተው አይንትራክት ክለብ የዘንድሮ የተጫዋቾች ዝውውር እንቅስቃሴን ከተመለከትን ክለቡን ለማጠናከር ወደ 11 ተጫዋቾች በውሰትና ግዢ ቡድኑን ሲቀላቀሉ ለዚህም 16.2 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጓል። ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ሆላንዳዊው ተከላካይ ጂትሮ ዊሊያምስ (5 ሚ.ዩሮ) ሲሆን 3 ተጫዋቾች በውሰት እንዲሁም 2 በነፃ ዝውውር ክለቡን የተቀላቀሉ ናቸው። ኮቫች በአዲሱ ሲዝን አልጠቀምባቸውም ብሎ ከክለቡ ካሰናበታቸው 14 ተጫዋቾች ሽያጭ 4.5 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ካዝናው ማስገባት እንደቻለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

 

Love Ethiopia!

 

One thought on “Ethiopia

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s